Teaser in Amharic

‹‹አንድ ነጠላ ታሪክ የተሳሳተ ምልከታዎችን እንዲፈጠሩ ያደርጋል፡፡  የተሳሳቱ ምልከታዎች ችግራቸው ስህተት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ያልተሟሉ ጭምርም መሆናቸው ናቸው፡፡ አንድን ታሪክ ብቸኛው ታሪክ ያደርጉታል፡፡ (…) ብዙ ታሪኮች ዋጋ አላቸው››  (ቺማንዳ ንጎዚ አዲቺ፣ ቴድ ቶክ 2009)

ብዙ ታሪኮች፣ ሰዎች ታሪኮቻቸውን እራሳቸው እንዲናገሩ በማድረግ የአፍሪካን የተለየ ዘርፈ ብዙ ገጽታ ለማሳወቅ የተዘጋጀ መድረክ ነው፡፡

ናይጄሪያዊቷ ደራሲ  ቺማንዳ ንጎዚ አዲቺ በቴድ የንግግር መድረክ ላይ በ2009 ዓ.ም ላይ እንደተናገረችው፣ የማህበረሰብን እውነታ እና በአንድ ብቸኛ አውነት፣ ‹ነጠላ ታሪክ› ላይ ብቻ የተንጠለጠሉ ሰዎችን ለመቀነስ ከመሞከር ይልቅ፣ ከእውነታ በራቀ እና ባልተሟላ ታሪክ በተቃራኒ የሚቆሙ ‹‹ብዙ ታሪኮችን›› ከተለያዩ አቅጣጫዎች መተረክን ታበረታታለች፡፡ በውጭ ሀገር የሚገኙ የጀርመን ተቋማት ውስጥ በፈቃደኝነት አገልግሎት የምንሰጥ በዩጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ኢትዮጵያ እና ኬኒያ የምንገኝ እኛ፣ በእዚህ ጉዳይ ላይ የራሳችንን አስተዋፅኦ ለማበርከት ፈልገናል፡፡ ማቅረብ የፈለግነውም የራሳችንን ምልከታ እና የህይወት ገጠመኝ ሳይሆን፣ በየሀገራቱ ያሉ ሰዎች የራሳቸው አመለካከት ላይ ትኩረት እንዲደያርጉ በማድረግ፣ እራሳቸው የራሳቸውን ታሪክ እንዲናገሩ ማስቻል ነው፡፡

 

‹‹ታሪኮች እንዴት ይተረካሉ፣ ሲተረኩስ ማን ነው የሚተርካቸው፣ ምን ያህል ታሪኮችስ ይነገራሉ – የሚሉት ጥያቄዎች በእርግጥ በባለቤቱ ስልጣን ላይ ጥገኛ የሆኑ ናቸው፡፡››  (ቺማንዳ ንጎዚ አዲቺ ቴድ ቶክ 2009)

ለእኛም የታሪኩ ባለቤት ባለስልጣንነት ግልፅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የብሎጉ ባለቤት እንደመሆናችን መጠን በምን ርዕሰ ጉዳይ ላይ ታሪኩ መቅረብ እንዳለበት የራሳችንን ተጽእኖ ማሳረፋችን አይቀርም፡፡